top of page

ዶክተር አሎን ሰካት የዓይን ህክምና ልዩ ባለ ሙያ ናቸው።  ከሁሉም በላይ በላቀ ሁኔታ በግሎኮማና ካታራክት ህክምና ዘርፍ ስልጥነው  ከፍተኛ እውቀት አላቸው።  ከፍተኛ እውቀት ያካባቱ የህክምና ዶክተር ባለ ሙያ ስለሆኑ በቴል ሃሾሜር "ሺባ" ሆስፒታል በዓይን ህክምና ክፍል ለህሙማን የዓይን ቀዶ ህክምና አርዳታ ያበረክታሉ። እንዲሁም በቴላቢብ ከተማ በሚገኘው በሳክለር ሥም በተሰየመው ዩኒበርሲቲ ህክምና ት/ቤት ያስተምራሉ። በእሥራኤል ሀገር የዓይን ሀኪሞች ማህበር የአስተዳደር ክፍል አባል ናቸው።
በራማት ሃሻሮን ከተማ በርሆብ ኦሲሽኪን 5 (3ኛ ፎቅ) በሚገኘው ጤና ጣቢያቸው ህሙማን እየተቀበሉ ያክማሉ። 

ዶክተር ሰካት ከ2000 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም በሳክለር ስም በተሰየመው በቴላቢብ ከተማ በሚገኘው ዩኒበርሲቲ ህክምና ት/ቤት ተማሩ። በዓይን ህክምና ዘርፍ ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት በቴል ሃሾሜር "ሺባ" ሆስፒታል በዓይን ህክምና ክፍል የሙያ እውቀት ማዳበሪያ ሥልጠና ተቀብለዋል። ዶክተር አሎን በዓይን ህክምና ከሁሉም የላቀ እውቀት ስላላቸው የአገር አቀፉ የዓን ህክምና ባለ ሙያዎች ማህበር የምስጉን ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

ከ2013 ዓ.ም እስከ 2015 ዓ.ም በአሜሪካ ውስጥ በኒወርክ ከተማ ማንሄተን በሚገኘው New York Eye & Ear Infirmary of Mount Sinai ምርጥና ጥራት ብቃት ባለው ተቋም በገለኦኮማ እና በካታራክት የዓይን ህክምና ዘርፍ ተምሮ የላቀ እውቀት አካብቷል። ዶክተር አሎን የሰለጠኑበት የዓይን ህክምና ተቋም በዓለም በመሪነት ደረጃ የሚገኝ ተቋም ሲሆን ያስተማሩት ምሁራን ፕሮፌሰር ሮበርት ሪች እና ፕሮፌሰር ጃፍሪ ሊብማን ናቸው። በአሚሪካ ኒወርክ ከተማ በሚገኘው የዓይን ህክምና ተቋም ትምህርቱን በተከታተለበት ወቅት ገለኦካማ እና ካታራክት የበተሰኙ የዓይን ህመም ዓይነቶች ከሁሉም በላይ የተሻሻለ ህክምና እርዳታ አሰጣጥ ዘዴና ስለ ዓይን የቀዶ ህክምና እርዳታ አሰጣጥ ዘዴ ሰልጥኗል። በሙያው የውቀት አድማሱን ለማሰፋት በአሜሪካ የህክምና ተቋም በሰራባቸው ወቅቶች በመላው አሜሪካ ከተለያዩ ግዛቶችና ከዓለም ሀገራት  የሚመጡ በባድ የዓይን በሽታ የተጠቁ ህሙማን በማከም  በህክምና ሙያ ታላቅ እውቀት በማካበት የቀዶ ህክምና እርዳታ በመስጠትና በጣም ውስብስብ በሆኑ የተለያዩ ህክምና ዘርፎች በብቃት ልምድን አካብተዋል።

ዶክተር ሰከዓት ከህክምና ሙያ ሥራቸው ጎን ለጎን በዓይን ህክምና ዘርፍ በተለይ በጋሎኮማ በሽታ ዓይነት በርካታ ጥናትና ምርምር አድርገዋል። የእሳቸው ጥናት ምርምር ውጤት በአለም ሀገራት እውቅናን ባተረፉት በሳይንሳዊ ምርመር ውጤቶች ወቅታዊ መጽሄቶች ላይ ለአንባቢያን ይፋ ሆነዋል። እሳቸው ስላደረጓቸው ጥናትና ምርምሮች በዓለም አቀፋዊ በርካታ ጉባኤዎች ተገኝተው ገለጻ እንዲያደርጉ ይገበዛሉ። 
ዶክተር አሎን ሰከዓት  IOSበተባለው የእሥራኤል የዓይን ሀኪሞች ማህበር ዓባል ናቸው። እንዲሁም American Academy of Ophthalmology በተባለው የአሜሪካ የዓይን ህክምና ባለ ሙያዎች ማህበርና በእስራኤል የጋላኮማ ሀኪሞች ቡድን ፤ በአሜሪካ የጋላኮማ በሽታ ልዩ ሀኪሞች ማህበር American Glaucoma Society ፤ በእሥራኤል የዓይን በሽታ ተመራማሪዎች ማህበር ISVER ፤ በአሜሪካ የዓይንና የመየት ምርምር ተቋም ማህበር ARVO ፤  በዓለም አቀፉ የጋላኮማ ድርጅት World Glaucoma Association ዓባል ናቸው።

 

የዶክተር አሎን ሳከዓት ርእዩተ ዓለም አመለካከትና ንግግር

'"ኔ የህክምና ሙያን መሰረት በማድረግ የእያንዳንዱን ታካሚ ችግሮች ለይቶ በማወቅ አስተማማኝ የሆነ ህክምና እና የቀዶ ህክምና እርዳታ ለማበርከት ቃል እገባለሁ። በሀኪሙና በታካሚው መካከል ግልጽ የሆነ ግንኙነት እና ትግስት በተቸረው መልካም ግንኙነት አምናለሁ። በተለይ ታካሚውን በመላካም ጸባይ መቀበል በጣም አስፋላጊ መሆኑን አምንበታለሁ።

በህክምናው ዘርፍ የአለምን የማጣሪያ መስፍርቶች ወይም ክራይቴሪዮች በማሟላት ለታካሚዎች ጥራትና ብቃት ያለው የህክምና እርዳታ ለማበርከት ቃል አገባለሁ። በህክምናው ዘርፍ የሚታዩትን ትሃድሶ ለውጦች ፤ አዳዲስ ግኝቶች ፤ አዲስ ተቀምመው ጥቅም ላይ የሚውሉ መዳህኒቶችን  እና በዘርፉ ያሉትን የቀዶ ህክምና ዘዴዎች መሰረት ያደረገ ህክምና እርዳታ ለታካሚዎች የመስጠት ታላቅ ኃላፊነት አለብኝ"።  

bottom of page